Addis Ababa

የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር

ስፖርት ለሁሉም

ድርጅታችን

የጤና ስፖርት የግለሰቦችን ጤና ከመጠበቅም በላይ ለሀገር እድገት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ያደጉት ሀገራት በጤና ስፖርት ዘርፍ ሀገርን የሚወክሉ የጤና ስፖርት ብሔራዊ ቡድኖችን ከ35 ዓመት በላይ በሆኑ ግለሰቦች መስርተዋል፡፡

የአዲስ አበባ የጤና ስፖርት ማህበር በኢትዮጵ ያየተቋቋመ የመጀመሪያው የጤና ማህበር ሲሆን ከተመሰረተ እነሆ 24 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ማህበሩ ከተቋቋመ ጀምሮ በርካታ የስፖርት ፍቅር ና ዝንባሌ ያላቸውን የህብረተሰ ብክፍሎችን በተለያየ ምድብ ከፍሎ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በብቃት እየተወጣ ይገኛል፡፡እድሜያቸው ከ35 ዓመትበላይየሆኑግለሰቦችንበማካተት፤ እነዚህ ለሀገር መጠቀም የሚችሉ ዜጎችን ከአልባሌ ሱስና ከአላስፈላጊ ስብዕናዎች እንዲሁ ምከተለያዩ ዓይነት በሽታዎችና ጭንቀት በመጠበቅ ረገድ ለህዝብና መንግስት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የማህበሩ ዋና እሴቶች

ማህበራዊ ግዴታ

የአዲስ አበባ ጤና ማህበር ማህበራዊ ኃላፊነቶቻቸውን ለመወጣት እየሞከረ ነው ፡፡ ለስፖርት አመሰግናለሁ; አባላቶቻችን በአደገኛ ሱስ ተጠቂዎች አይደሉም ፡፡

ጓደኝነት

አዲስ ፊት ለመገናኘት እና የዕድሜ ልክ ጓደኞች ለመሆን ትልቅ እድል አለ ፡፡

የፍርድ ቤት እና ሙግት

የጤና ስፖርት ማህበር የምንግዜም ተልዕኮው የአባላቱን ጤና በስፖርት መጠበቅ ነው፡፡ ማህበሩ እንደ ራዕይ የያዛቸው፤

ስለ አመሰራረታችን

የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር የተመሰረተው በ 1986 ዓ.ም ሲሆን የአማኑኤል የጤና ቡድን በ1986 ዓ.ም  ከስካኒያ የጤና ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ያቀረበው ግብዣ ተቀባይነት አግኝቶ ታሪካዊውን ጨዋታቸውን በአማኑኤል የጤና ቡድን ሜዳ ላይ ማድረጋቸው ዛሬ በአድናቆት ለምናየው የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር መቋቋም ምክንያት ሆኗል፡፡

የሁለቱ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የስካኒያ ቡድን በሲሚንቶ ፋብሪካ ሜዳ ላይ ለማድረግ ግብዣውን አቅርቦ የመልሱ ጨዋታ ከተደረገ በኋላ በቅሎ ቤት ጠመንጃ ያዥ ባንክ ፊት ለፊት በሚገኘው ሀረግ ሆቴል የምሳ ግብዣ ባደረገበት አጋጣሚ ታሪካዊ ውይይት ተካሄደ፡፡በዚህ ግብዣ ወቅት ከሁለቱም ቡድኖች አንድ አንድ አባላት በሞት መለየታቸው ይነሳና ሁለቱ ቡድኖች ሁለት ሁለት ቡድኖች ይዘውና ሌላ ተጨማሪ ሁለት ቡድኖች ፈልገው በማካተት የመታሰቢያ ውድድር ለማድረግ የሚችሉበትን መንገድ የሚፈጥሩበት ሁኔታ እንዲኖር ሀሳብይ ቀርባል፡፡ይህ ሃሳብ በሁለቱም የቡድን አባላት ዘንድ ተቀባይነት በማግኘቱ ለተግባራዊነቱ እንቅስቃሴ የሚያደርግ አካል ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመታመኑ ከስካኒያ እና ከአማኑኤል የጤና ቡድኖች የተወከሉ አባላትን በማዋቀር የስራ ድርሻቸውን እንዲከፋፈሉ በማድረግ ስራው በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ተደርጎ የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር መሰረት ተጣለ፡፡

የእኛ ወሰን

የአዲስ አበባ የጤና ስፖርት ማህበር በኢትዮጵ ያየተቋቋመ የመጀመሪያው የጤና ማህበር ሲሆን ከተመሰረተ እነሆ 24 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ማህበሩ ከተቋቋመ ጀምሮ በርካታ የስፖርት ፍቅር ና ዝንባሌ ያላቸውን የህብረተሰ ብክፍሎችን በተለያየ ምድብ ከፍሎ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በብቃት እየተወጣ ይገኛል፡፡እድሜያቸው ከ35 ዓመትበላይየሆኑግለሰቦችንበማካተት፤ እነዚህ ለሀገር መጠቀም የሚችሉ ዜጎችን ከአልባሌ ሱስና ከአላስፈላጊ ስብዕናዎች እንዲሁ ምከተለያዩ ዓይነት በሽታዎችና ጭንቀት በመጠበቅ ረገድ ለህዝብና መንግስት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ማህበሩበ ስሩ 43 የጤና ቡድኖችን ያካተተ ሲሆን በፍቃደኛ እና ለጤና ስፖርት ትኩረት በሰጡ ታታሪ የረጅም ጊዜ አባላት እየተመራ ነው፡፡ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ያስመዘገባቸው ስኬቶች የአባላቱን ጥንካሬና የአመራሩን ሩቅ አሳቢነት ያሳያል፡፡

0 +
ከ35 አመት በላይ
0 +
ከ40 አመት በላይ
0 +
ከ50 አመት በላይ